የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

Nested Applications

Asset Publisher

null የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

መጋቢት 19/2016 . (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የታክስ ሰርዓቱን ለማዘመን የወረቀት አሰራሮችን የሚያስቀር  የኤሌክትሮኒክስ ኢንቮይስ ሲስተም አስተዳደር  ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል ሰነድ  ከከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት  አስተዳደር ጋር ተፈራርሟል::

ስምምነቱን  የገቢዎች ሚኒስትር / አይናለም ንጉሴ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት  አስተዳደር  ዋና ዳይሬክተር / ትግስት ሀሚድ ፈርመዋል::

በስምምነቱ ላይ የገቢዎች ሚኒስትር / አይናለም ንጉሴ  በህገ ወጥ ንግድ በቀረጥ እና ታክስ ማጭበርበር ምክንያት የኢትዮጽያ ኢኮኖሚ መሰብሰብ ያለበትን ገቢ ለመሰብሰብ አለመቻሉን አመላክተው ይህ ስርዓት  የግብይት ደረሰኝን ከአንድ አካል ብቻ ማለትም ከገቢዎች ሚኒስቴር ብቻ እንዲቆረጥ በማድረግ በሃሰተኛ ደረሰኝ የሚደረግ ማጭበርበርን የሚያስቀር ነው ብለዋል::

ሚኒስትሯ  ስርዓቱ ለነጋዴው ማሕበረሰብም ሆነ ለሸማቹ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረው የነጋዴው ማህበረሰብ ለደረሰኝ ሕትመት የሚያወጣውን ወጪና ጊዜ ከማስቀረቱም በላይ የግብይት ሂደቱን በቀጥታ ለመከታተልና ለመቆጣጠርም እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት  አስተዳደር  ዋና ዳይሬክተር / ትግስት ሀሚድ በበኩላቸው የሚዘረጋው  የኤሌክትሮኒክስ ኢንቮይስ ሲስተም  ስርዓት የማንዋል የደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ወደኤሌክትሮኒክስ የደረሰኝ አስተዳደር ስርአት ለመቀየር የሚያስችል እንዲሁም የዲጂታል ግብይት ስርአቱን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳልጥ   መሆኑን አንስተው የሚዘረጋው ስርዓት ውጤታማ እንዲሆን የተቻለው ጥረት ሁሉ እንደሚደረግም ተናግረዋል::

Asset Publisher

null የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

መጋቢት 05/2016 . (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ለማዘመን በሚያስችል ረቂቅ ሰነድ ዙሪያ ከታክስ ትራንስፎርሜሽን /ቤት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለግብር ከፋዮች ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ነው ያሉት የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ / መሰረት መስቀሌ ሆኖም አጠቃላይ የታክስ ስርዓቱን ከማዘመን አኳያ ብዙ መስራት እንደሚጠይቅ ገልፀዋል፡፡

ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት በተከናወኑ በርካታ ስራዎች ከዓመት ዓመት የሚሰበሰበው ታክስ እያደገ ቢመጣም ከአህጉራዊና ዓለማቀፋዊ መለኪያዎች ጋር ሲነጻጸር ብዙ መስራት እንደሚጠይቅ በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ለዚህ ደግሞ አጠቃላይ የታክስ ስርዓቱን ማዘመንና በታክስ አስተዳደሩ ዙሪያ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት አሰራሮችን በቴክኖሎጂ ማስደገፍ የፖሊሲ ማሻሻያ የሚያስፈልጓቸው የታክስ ህጎችን መፈተሽ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለው አንስተዋል፡፡

በውይይቱ የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ችግሮችን በመለየት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ በማድረግ የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የኢ-ታክስ እና -ፋይሊንግ አሰራርና አጠቃቀምን በማሻሻል ረቂቅ ሰነዱ ተጠናቆ ወደ ተግባር ሲገባ የታክስ አስተዳደሩን በማዘመን የገቢ አሰባሰቡን እንዲያድግ ያስችላል ተብሏል፡፡

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.