የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ
የገቢዎች ሚኒስቴር የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አሰጣጡን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል ፡፡
ስምምነቱን የገቢዎች ሚኒስቴር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ፈርመዋል፡፡
በእለቱ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ስምምነቱ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አሰጣጥ ሂደት የሚሰተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ለግብር ከፋዮች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡ ተቋሙ ለግብር ከፋዮች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለመስጠት ለቴክኖሎጂ ግዥ የሚያወጣውን ወጭ በማስቀረትም ሀገራችን የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ይርዳል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለውም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ሀሰተኛ ማንነትን መስረት በማድረግ የሚፈፀሙ ማጭበርበሮችንና ወንጀሎችን በቀላሉ ለመከላከል ስለሚረዳ የሀገራችን ኢኮኖሚ እንዳይመዘበር ይርዳል ብለዋል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮገራም ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል በበኩላቸው የገቢዎች ሚኒስቴር ለሀገር አለኝታ የሆነውን ግብር የመሰብሰብ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስፈላጊውን ድጋፍ የደርጋል ብለዋል፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር በቅርቡ እንዲተሳሰር በማድረግ ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል፡፡
በብዛት የተነበቡ ዜናዎች
-
Fri, 29 Oct 2021"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
-
Wed, 4 Jan 2023"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)